የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎችን ሹመት አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የቀረበውን የተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል፡፡

ሹመቶቹም እንደ አዲስ በተቋቋሙ እና ማሻሻያ በተደረገባቸው ተቋማት ላይ የተሰጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚሁም መሰረት፡-

1. አቶ እንዳወቅ አብቴ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

2. ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ – የባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ ጀማሉ ጀንበር – የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ ኃይለሰማያት መርኃጥበብ – የወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ቢሮ ኃላፊ

5. አቶ ዮሐንስ ምትኩ – የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ

6. ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ – የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

7. ወ/ሮ ፍሬህይወት ተፈራ – የአቃቤ ህግ ቢሮ ኃላፊ

8. አቶ አብዱልፈታ ዮሱፍ – የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡

 

ምክር ቤቱ በተጨማሪም ለአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት የቀረቡትን አዳዲስ አመራሮች ሹመት አፅድቋል፡፡

በዚህም መሠረት፦ 
1. አቶ ተስፋዬ መለሰ – የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ፕረዝዳንት

2. ወ/ሮ ፍራኦል ቶሎሳ – የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ምክትል ፕረዝዳንት በመሆን ተሹመዋል፡፡ (ምንጭ፡-የከንቲባ ጽህፈት ቤት)