ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኡምሀጅር-ሁመራ ድንበር መንገድን በይፋ ከፈቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮ-ኤርትራ ኡምሀጅር-ሁመራ ድንበር መንገድን በይፋ ከፈቱ፡፡

የድንበሩ መከፈት የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች ግንኙነትን እንደሚያጠናክር ተገልጿል፡፡  

በስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ኤርትራ ተሰኔ ሲገቡ፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በኤርትራ በኩል በተሰንዓና ጋርሴት÷ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ በኡምሀጅር-ሁመራ ድንበር እየተካሄዱ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረገው ጥረት አካል ነው።(ምንጭ: ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት )