ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር ጋር ተወያዩ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር ሊዮ ቫራድካር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራዳር በውይይታቸው ወቅት ኢትዮጵያ በተለይ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮና የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን ያከናወነቻቸው ተግባራት በዓለም ደረጃ አድናቆትን እንዳስገኘላት  አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛዋ የአየርላንድ የልማት አጋር መሆኗን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቸው ይህንን አጠናክሮ ለመቀጥልና በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በበኩላቸው አየርላንድ በግብርናና በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ የከብት ልማት ያላት በመሆኑ አገራችንም አያሌ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ላይ ያለች መሆኗን ጠቅሰው በርካታ የአየርላንድ ኢንቨስተሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጋብዘዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ስለአየርላንድና አፍሪካ ግንኙነት፣ ስለተመድና አየርላንድ የጸጥታው ምክር ቤት እጩነትዋ ላይ ተወያይተዋል፡፡ (ምንጭ፡-የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት)