የጀርመን ፕሬዚዳንት በያዝነው ወር መጨረሻ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜር በዚህ ወር መጨረሻ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡

ፕሬዚዳንት ፍራንክ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

በጉብኝታቸውም ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ፍራንክ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናትትንም ይጎበኛሉ ነው የተባለው፡፡

ኢትዮጵያና ጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ከ100 ዓመታት በፊት በ1905 እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ሁለቱ ሀገራት  በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ፣  በግብርናና በኢንቨስትመንት መስክ በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በአበባ ልማት ዘርፍ ላይም 35 የሚሆኑ የጀርመን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡  (ኤፍ.ቢ.ሲ)