የመገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ትስስር ገጾች በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የበኩላቸውን ተገቢ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ተገለጸ

በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች በአገሪቱ  ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የበኩላቸውን ተገቢ ሚና  ሊጫወቱ   እንደሚገባ  የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች  ማህበር ( ኢጋማ) አስታወቀ  

ማህበሩ  በዛሬው ዕለት  በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና በማህበራዊ ሚዲያዎች እየታዩ ያሉና  የጥላቻ  እንዲሁም ጠብ አጫሪ  ቃላት  አላስፈላጊ እንደሆነ አመልክቷል

የመንግሥትም ይሁን የግል መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች  ከፖለቲካዊ ውግንና በመራቅ የገለልተኝነት፣ ሚዛናዊነት ፍትሃዊነት ሙያዊ መርሆችን ሳይሸራረፉ  በቁርጠኝነት  ተግባራዊ ማድረግ  እንደሚገባቸው  መግለጫው ጠቁሟል    

በተለያዩ የአገሪቱ  አካባቢዎች እየታዩ ባሉት የእርስ በእርስ ግጭቶች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይባባሱም  የመገናኛ ብዙሃንነ የማህበራዊ ትስስር  ባለሙያዎች የበኩላቸዉ ሚናና ኃላፊነት   በመወጣት  እንደሚገባቸው መግለጫው ጠቅሷል፡፡

ጋዜጠኛ ለህዝብ ሰላም ወግኖ መንቀሳቀስ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ኃላፊነት መሆኑንና የዜግነት ድርብ ሃላፊነት መሆኑን ሁሉም ሊረዳው እንደሚገባ  የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር (ኢጋማ) ገልጿል ፡፡

ሆኖም አንዳንድ  የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊነት መልኩ  ግጭት ቀስቃሽ፣ ጥላቻና ጠብ አጫሪ  ዘገባዎችን  ሲቀርቡ እንደሚስተዋል  መግለጫው አትቷል  ፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር 50 አመቱ ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑን  በመግለጫው ተመልክቷል፡፡