የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሰኞ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ገለጸ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጭው ሰኞ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ገለጸዋል፡፡

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በስብሰባው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ሂደት ላይ ይመክራልም ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎም ነው የሚጠበቀው። (ኤፍ.ቢ.ሲ)