ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን ገቡ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን ገብተዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሴራሊዮን ፍሪታውን እንደደረሰ በሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ የጉብኝት ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ነው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያስታወቀው፡፡

ልዑኩ በሁለት ቀናት ቆይታው ከሴራልዮን መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ህብረ-ዘርፋዊ ትብብር ዙሪያ የሚመካከር ሲሆን በመጨረሻም የጋራ መግባቢያ ሰነዶች እንደሚፈራረም ይጠበቃል፡፡

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝቱ የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ባደረጉላቸው ግብዣ ነው፡፡ (ምንጭ፡-የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)