የደኢህዴን ወጣቶች ሊግ መደበኛ ጉባኤ ይካሄዳል

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ ወጣቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል

ጉባዔው “ምክንያታዊ ወጣት ለሃገራዊ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል ከጥር 14 እስከ 16 2011 በሃዋሳ እንደሚካሄድ የደኢህዴን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሃላፊ ወጣት ዘመን ተሰፋዬ ገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ ሊጉ ባለፉት ሶስት አመታት የወጣቱን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት ይዳሳሰሉ፡፡

በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮችን በመገምገም አሁን በሃገሪቱ እየመጣ የሚገኘውን ለውጥ ወጣቱ በባለቤትነት ማስቀጠል እንዳለበት እንሚመክርም ወጣት ዘመን አስረድቷል፡፡

በተጨማሪም ጉባዔው የቀጣይ ሁለት አመት ተኩል አቅጣጫን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡