ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፓ የሚያደርጉትን ገብኝት በዛሬው እለት ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከልዑካን ቡድናችው ጋር በመሆን የአውሮፓ ጉብኝታቸውን መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በቆይታቸው በስዊዘርላንድ ዳቮስ በሚካሄደው የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ መድረክ ላይ በመሰተፍ ንግግር እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ከዚህ ጎን ለጎን ከተለያዩ የአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ተብሎ እንደሚጠበቅም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።