ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጣሊያን ሮም ገቡ

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመራ ልዑካን ቡድን በአውሮፓ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ጣሊያን ሮም ከተማ ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ሮም ከተማ ሲደርሱ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሮም ቆይታቸው ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ እና ከልማት አጋሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በ2011 ዓ.ም መጀመሪያ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጣሊያንን እንዲጎበኙ መጋበዛቸው ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)