የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ

የአማራ ዴሞክራሲያ ፓርቲ /አዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ጀምሯል ።   

ማዕከላዊ ኮሚቴው በመደበኛ ስብሰባው ካለፈው ድርጅታዊ ጉባኤ በተሸጋጋሩ  አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ነው ተብሏል።

ከአጀንዳዎች መካከልም አዲስ የድርጅቱን አርማ እና የድርጅቱ ልሳናት እጣ ፈንታ ላይ መወያየት ይገኝበታል።

በተጨማሪም በክልሉና በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉትን የለውጥ እርምጃዎች በመመልከት እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በጥልቀት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል።