ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሮማው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሮማው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ባለፈም ከቫቲካን ዋና አስተዳዳሪ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋርም ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያና በቫቲካን የጋራ ፍላጎቶች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻ ቀን የሮም ቆይታቸው በቫቲካን የሚገኘውን የቅዱስ እስጢፋኖስ የአቢሲኒያ ቤተክርስቲያንን ጎበኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ አነሳሽነት የተገነባውን የሰላም ድልድይ ያስታወሱት ካርዲናል አባ ብርሃነ ኢየሱስ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ወደጣሊያን ማቅናታቸው የሚታወስ ነው።

በቆይታቸውም ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። 

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጋር ባደረጉት ውቅይይትም በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም ከተለያዩ የልማት አጋር መሪዎች ጋር በተናጠል ውይይት አድርገዋል።(ኤፍቢሲ)