የደኢህዴን ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በሐዋሳ እየተካሄደ ነው

የደኢህዴን ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው ምክኒያታዊ ወጣት ለሀገራዊ ለውጥ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከፊታችን ጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ይካሄዳል።

የዘንድሮው የወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 እስከ ጥር 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ይሆናል።

ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች የሊግ ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሚካሄድ ይሆናል።

ጉባኤው በ3ኛው መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግና አፈጻጸማቸውን በመገምገም፥ ጥንካሬዎች የሚጎለብቱበትና እጥረቶች የሚታረሙበት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡(ምንጭ:  የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት)