ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት ጋር በመጪው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታችው ተገናኝተው ተወያይተዋል።

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ከየካቲት 3 እስከ 4፤2011 “ስደተኞች፣ ከስደት ተመላሾችና ተፈናቃዮች፤ በአፍሪካ በግድ መፈናቀል ለማስቆም ዘላቂ መፍትሄ እንፈልግ” በሚል መርህ ይካሄዳል።

ሁለቱ ወገኖች ጉባኤው ከተለመደው መንገድ ለየት ባለ መልኩ ሊከናወን በሚችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተነጋግረዋል።

በተጨማሪም የጉባኤው አጀንዳ የህብረቱ የለውጥ አሰራር በአፍሪካውያን ህይወት ላይ እንዴት ትርጉም ያለው ተፅእኖ እንደሚያስከትል በበቂ እንዲያስተገባ ተስማምተዋል።

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት በዴሞክረሲያዊ የኮንጎ ሪፐብሊክ ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል። (ምንጭ:- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)