ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ የተለያዩ ሹመቶች ሰጡ

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዩ የመንግስት ሀላፊነት ቦታዎች ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት መረጃ መሰረት፡- 

1.አቶ ፍራኦል ተፈራ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

2.አቶ ማተቤ አዲስ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር 
3.አቶ እዮብ አወቀ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

4.ዶክተር መብራህቱ ገ/ማሪያም የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

5.አቶ መስፍን ነገዎ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

6.አቶ እስማኤል አሊሴሮ በሚንስትር ዴኤታ ማእረግ የሰላም ሚንስትር አማካሪ

7.አቶ ታምሩ ግንበቶ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር 
ሆነው ተሹመዋል፡፡