አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልቀቂያ አቀረቡ

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው ጥያቄውን ያቀረቡት።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የርዕሰ መስተዳድሩን ጥያቄ ተቀብሎታል።

የመልቀቂያቸውን ምክንያትም አዴፓ ለአማራ ክልል ምክር ቤት እያቀረበ ነው።

በቀጣይም ምክር ቤቱ መልቀቂያውን ተቀብሎ አዲስ ርዕሰ መስተዳድር እንደሚሾም ይጠበቃል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልልን ከታኅሳስ 2006 ዓ.ም ጀምሮ በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል።

ዶክተር አምባቸው መኮንን ለርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡