ዶክተር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

​​​​​​የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶክተር አምባቸው መኮንንን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡

ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው እለት መልቀቂያ አስገብተው መልቀቂያቸው ተቀባይነት በማግኘቱ ነው ዶክተር አምባቸው የተሸሙት፡፡

ዶክተር አምባቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

ከዚህ ባለፈም የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው።