ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ትስስር ለማጠናከር የጀመረችው ጥረት ጠንካራ አህጉር ለመገንባት እንደሚያግዝ ተገለጸ

የኡቡንቱ ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት መሥራች አቶ ዮሐንስ መዝገበ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ትስስር ለማጠናከር የጀመረችው ጥረት ጠንካራ አህጉር ለመገንባት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ አገራዊ ለውጥን መተግበር ከጀመረች የአንድ አመት ያህል ዕድሜ ያስቆጠረች ሲሆን በቀጠናው እያከናወነች ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የገለጹት አቶ ዮሐንስ ይህም የአፍሪካ ሀገራት በምጣኔ ሀብት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ትስስራቸው እንዲጠናከር ያስችላል ነው ያሉት፡፡

ከምዕራቡ እና አረብ ሀገራት ያላትን ወዳጅነት በተለያዩ መስኮች ለማጠናከር መስሯቷም የውስጥ የልማት ጥያቄዎቿን በጋራ ጥቅም ትስስር ለመፍታት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ይህንን አገራዊ ለውጥና የውጭ ፖሊሲ ትግበራ አጠናክሮ ለማስቀጠልም መንግስት በትኩረት መስራት እንዳለበት አቶ ዮሐንስ አክለዋል፡፡