የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አምባቸው መኮንን የድርጅቱ ም/ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አምባቸው መኮንን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ምክትል ሊቀ-መንበሩን እና አዳዲስ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎችን መርጧል።  በዚህ መሰረት

1.አቶ ደመቀ መኮንን የአዴፓ ሊቀመንበር

2.ዶ/ር አምባቸው መኮንን ምክትል ሊቀመንበር

3.አቶ ላቀ አያሌው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ( አዲስ)

4.አቶ መላኩ አለበል የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

5.አቶ ምግባሩ ከበደ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

6.አቶ ዮሀንስ ቧያለው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ( አዲስ)

7.ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

8.አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

9.አቶ ብናልፍ አንዱአለም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

10.አቶ ተፈራ ደርበው የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

11.ዶክተር ይናገር ደሴ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

12. አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

13. አቶ ፀጋ አራጌ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው መመረጣቸውን ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡