ምክር ቤቱ በፌዴራል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ውይይት አደረገ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮን ለመወጣት እንዲችል ያሉበትን ውስንነቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በመለየት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሙሉ ጊዜያቸውን በቦርዱ ስራ የሚያሳልፉ ተሿሚዎች መሆናቸውን እና የቦርዱ የአመራር ሃላፊነት ከግምት በማስገባት የተሿሚዎች ቁጥር ከ9 ወደ 5 መቀነስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ለማጠናከር ምርጫ ቦርድን ከማናቸውም አካል ነጻ አድርጎ በማደራጀት ፍትሃዊ፣ ተአማኒ እና ሰላማዊ ምርጫ ለማስፈጸም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት አመላመል እና አሿሿም እንዲሁም የስራ አመራር የቦርድ አባላት አሰያየም አሳታፊነት እና ግልጸኝነትን አስመልክቶ በውይይቱ የተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ባለ ድርሻ አካላት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

(ምንጭ፡- የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት)