ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከኮንጎው አቻቸው ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኮንጎው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ተሺሰክዲ ጋር በሩዋንዳ ኪጋሊ ተወያዩ፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ነው የተወያዩት፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ7ተኛ ጊዜ በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ኩባንያ መሪዎች ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

(ምንጭ፡- ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት)