ማንኛውም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንደሚሰራ ኦዴፓ ገለጸ

ማንኛውም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) እንደሚሰራ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።

ፓርቲው የተመሰረተበት 29ኛ ዓመት በዓል የማዕከላዊ አባላቱ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተከብሯል።

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር፤ ዜጎች 'የኔ ነው' ከሚል መገፋፋት ወጥተው 'የእኛ' ወደሚል አብሮነት እንዲሸጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ለውጥ ሁሉ ፈተና እንዳለው ገልጸው፣ ፈተናውን በጋራ በመሰለፍ መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ያልተመለሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት ሁሉም መነሳት እንደሚጠበቅበትም አመልክተዋል።

(ምንጭ፡-ኢዜአ)