ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ፡፡

በዚሁ መሰረት ዶክተር አለሙ ስሜ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ጃንጥራር አባይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር፣ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን ከሚያዚያ 9፣ 2011 ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በተጨማሪም አቶ ገዛሃኝ አባተ ከሚያዚያ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።