የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከመ/ቤቱ አመራሮች ጋር የስራ ትውውቅ አደረጉ

አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋችው ከመስሪያ ቤቱ አመራሮች ጋር በዛሬው ዕለት ትውውቅ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በነበራቸው ቆይታ በመስሪያ ቤቱ ከሚገኙ ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ ቋሚ ተጠሪዎች፣ ዳይሬክተር ጄኔራሎችና የጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ጋር አጠቃላይ ትውውቅ አድርገዋል።

ከሰዓት በኋላ በነበራቸው ቆይታም በተቋሙ ከሚገኙ አህጉራዊ ዘርፎች ጋር የስራ ትውውቅና ዝርዝር ውይይቶችን አካሂደዋል።

በነገው እለትም በተመሳሳይ በተቋሙ ከሚገኙ የኢኮኖሚና ዳያስፖራ ዘርፎች፣ የስራ አመራርና የሰው ሀይል ዘርፎች እንዲሁም ከሌሎች ዘርፍ አመራሮች ጋር የስራ ትውውቅና ዝርዝር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል(ኤፍቢሲ)