ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ስለሱዳን በካይሮ በመከረው ጉባኤ ላይ ተሳተፉ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በማተኮር በግብፅ በተካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ተሳተፉ።

በዚህም መሪዎቹ የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እንዲያረጋግጥ የሶስት ወር ጊዜ እንዲሰጠው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የአፍሪካ ህብረት የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት በ15 ቀናት ውስጥ ስልጣኑን በሲቪሎች ለሚመራ የፓለቲካ ቡድን ካላስተላለፈ ከህብረቱ አባልነት ሀገሪቱን እንደሚያግዳት ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

በውይይቱ በተደረሰው ስምምነትም የሽግግር ምክር ቤቱ የ15 ቀናት እገዳ ሊራዘም ችሏል ነው የተባለው።

የግብፁ ፕሬዚዳንት ኤል ሲ ሲ በስብሰባው ማጠናቀቂያ መሪዎቹ በራሳቸው በሱዳናዊያን እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በአፋጣኝ ህገ መንግስታዊ ስርዓት እንደሚመለስ ስምምነት ላይ መደሱን ተናግረዋል።

ኤል ሲ ሲ እነዚህ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ለሱዳን ባለስልጣናት እና ፓርቲዎች ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥም ነው የተስማሙት።

ውይይቱ በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርና የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ ኤል ሲ ሲ ጋባዥነት ነው ተካሄደው። 

(ምንጭ፡- (ፍራንስ 24))