ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በጀርመን ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ገልፀዋል።

የቀብር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ ብሔራዊ ኮሚቴ የሚቋቋም ሲሆን፥ ዝርዝር ጉዳዮችን በየጊዜዉ የሚገለጽ ይሆናል ፡፡

ምንጭ ፡- ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት