8ኛው የጣና ፎረም በሳምንቱ መጨረሻ ይካሄዳል

8ኛው የጣና ፎረም በሳምንቱ መጨረሻ በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል።

ፎረሙ የፖለቲካ ሁኔታ ተለዋዋጭነት በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጅማሮዎችን ማስቀጠል በሚል መሪ ቃል የፊታችን ቅዳሜና እሁድ የሚካሄድ ይሆናል።

የዘንድሮው የጣና ፎረም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በቅርቡ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሚካሄድ ይሆናል።

ከዚህ አንጻርም የአፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ባለው የፖለቲካ ተለዋዋጭነትና ሰላምን ለማስፈን መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡

(ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)