ጠ/ሚ ዐቢይ የዩኔስኮን የ2019 የሰላም ሽልማት አሸነፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት ላደረጉት አስተዋፅኦ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት 2019 አሸናፊ ሆኑ፡፡

በአፍሪካ ህብረት እየተከበረ ባለው የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀን ላይ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር አድሪ አዙላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዘንድሮውን የድርጅቱ የሰላም ተሸላሚ መሆንን ይፋ አድርገዋል።

የላይቤሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እና የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎን የተካተቱበት የዩኔስኮ የተሸላሚዎች መራጭ ኮሚቴ ነው ምርጫውን ያከናወነው።

ሽልማቱ እንደአውሮፓውያ ዘመን ቀመር 1991 ጀምሮ ከ20 በላይ ለሚሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ተበርክቷል፡፡  

(ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት)