በኢትዮጵያ በሚዲያዉ ዘርፍ የተጀመረዉ ለዉጥና ማሻሻያ የሚደነቅ መሆኑን አለም አቀፍ ጋዜጠኞች ገለጹ

በኢትዮጵያ በሚዲያዉ ዘርፍ የተጀመረዉ ለዉጥና ማሻሻያ የሚደነቅ ነዉ ሲሉ በ26ኛዉ የአለም የሚዲያ ነፃነት ቀን ተሳታፊ የሆኑ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

26ኛዉ የአለም የሚዲያ ነፃነት ቀን ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ መካሄድም የሀገሪቱ መንግስት እያከናወነ ያለዉ የማሻሻያ ስራ በአለም መንግስታትና ተቋማት ዘንድ እዉቅና ማግኘቱን የሚያሳይ እንደሆነም ለዋልታ ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

የሚዲያ ምህዳሩን ይበልጥ ነፃ ለማድረግም ህግና ስርዓትን የተከተለ ተቋማዊ አሰራርን መከተል ይገባዋል ብለዋል ተሳታፊ ጋዜጠኞቹ።