አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍን ጎበኙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍን ጎበኙ፡፡

በዛሬው ዕለት በኢንተርፕራይዙ የተገኙት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

3 ግዙፍ ተቋማትን በስሩ የሚያስተዳድረው ኢንተርፕራይዙ አሁን ያለበትን የአፈፃፀም ብቃት በተመለከተ ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት በዘርፉ እየተሰራ ያለው ስራ የመከላከያ አቅምን በማሳደግ በኩል ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ኢንተርፕራይዙ ሰራዊቱን ለተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ ያለውን አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ የሰራዊቱን ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ፍላጎት ለማሟላት የተቋቋመውን የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽንን በተመለከተም ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በተጨማሪም በሰሚት እየተገነቡ ያሉ የመኖሪያ ቤቶችንም ጎብኝተዋል፡፡

(ምንጭ፡- የመከላከያ ሚኒስቴር)