ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኬንያ አቀኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኬንያ የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ጠዋት ወደ ኬኒያ ናይሮቢ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ በቆይታቸውም ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መረጃው የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ነው፡፡