ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ እና ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ እርቅ ማውረድ አለባቸው ተባለ

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) እና ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ህ.ግ.ሓ.ኤ) እርቅ ማውረድ አለባቸው  ተባሏል፡፡

ሰለብሪቲ ኤቨንትስ እንዳስታወቀው በኢትጵያ እና በኤርትራ የወረደው እርቅ በፓርቲዎች ሊደገም ይጋባልም ብሏል፡፡

የፓርቲዎቹ እርቅ፤ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠንከር ስለሚበጅ ሰለብሪቲ ኤቨንትስ የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑንም ይፋ አድርጓል፡፡

የእርቀ ሰላም ጉዞ እንዲሳካ ለሁለቱ አገራት ሕዝብ እና መንግስት ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ መቅርቡም ሰለብሪቲ ኤቨንትስ ለዋልታ በላካው መግለጫ አትቷል