የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ አገራዊ አጀንዳዎች ላይ እየተወያዩ ነው

በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት ቀደም ብሎ በፓርቲዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት በዛሬው ዕለት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በወቅታዊ አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱም የኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት ተቃርኖዎች መንስኤዎችና ውጤቶች፣ የሰላም ምንነት አስፈላጊነትና የባለድራሻዎች ሚና፣ የለውጡ ምንነት አስፈላጊነትና ፈተናዎችና መፍትሔዎች እና በማህበራዊ ተሳትፎ ምንነት አስፈላጊነትና መልኮቹ በሚሉ ርዕሶች ላይ ያተኩራል፡፡

የውይይት መድረኩን ወይዘሮ ቆንጅት ብርሃን የሚያስተባብሩት ሲሆን፣ የመነሻ ጽሑፍ አቅራቢዎችም ዶክተር ሰሚር አሚን፣ ፕሮፌሰር እዝቅያስ አሰፋ፣ ዶክተር ኤልሳቤጥ ሀይለጊዮርጊስ እና አቶ አንዷለም አራጌ ናቸው፡፡