2ኛው የመቶ ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሁለተኛውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄዱ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፖሊሲና የአፈጻጸም ክትትል ቡድን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ግምገማዎችን አድርጓል።

ግምገማው የተቋማቱን ሪፖርት በመገምገም፣ ከተቋማቱ ጋር ውይይት በማካሄድና በድንገት ጉብኝት በማድረግ እንዲሁም ከተጠቃሚዎችና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት መረጃዎችን በመሰብሰብ ማካሄዱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የመጀመሪያው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከሶስት ወራት በፊት መካሄዱ የሚታወስ ነው።