ለጋዜጠኞችና ጦማሪያን የግጭት አዘጋገብ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ጦማሪያን ግጭትን እንዴት መዘገብ እንዳለባቸዉና ለሰላም የሚያበረክቱትን ድርሻ በሚመለከት በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የሰላም ሚንስቴርና ጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ አገር በቀል መንግታዊ ያልሆነ ድርጅት በጋራ በመሆን ስልጠናውን አዘጋጅተዉታል፡፡

የሰላም ሚንስቴር ሚንስቴር ዲኤታ አልማዝ መኮንን ስልጠናውን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የህዝብ አይንና ጆሮ በመሆናቸዉ የማህበረሰቡን እሴት በማጎልበት ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያቀራርቡ አጀንዳዎች ላይ መስራት አለባቸዉ፡፡

ስልጠናዉ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡