የእነጌታቸው አሰፋን የፍርድ ቤት መጥሪያ ትዕዛዝ ማድረስ አልቻልኩም – ፌዴራል ፖሊስ

በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ያለው እነጌታቸው አሰፋ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የተሰጠው የመጥሪያ ትዕዛዝ በጊዜ ከፍርድ ቤት ባለመውጣቱ ማድረስ አልቻልኩም ሲል የፌደራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ መጥሪያ እንዲደርሳቸው በድጋሜ በግምቦት ስምንት የተላለፈው የችሎት ትዕዛዝ የፌደራል ፖሊስ የደረሰው ከሁለት ቀናት በፊት ማለትም ግምቦት 14 እንደሆነ በገለፀበት ማመልከቻው መጥሪያውን ለተከሳሾች ለማድረስ ተለዋጭ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ተከሳሾች ያሉበት ትግራይ ክልል በመሆኑን ከርቀቱ አኳያ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት ምክንያት አቅርባል፡፡

በችሎቱ አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም በነበሩ ሁለት ችሎቶች አቅርብ የተባለውን የሲዲ ማስረጃ ሲታተም ከተዘለለ አንድ ሲዲ በስተቀር ለችሎትና ለተከሳሾች አድርሷዋል፡፡

ሲታተም የተዘለለ እንድ የሲዲ ማስረጃ በቀጣይ የችሎት ውሎ አባዝቶ እንደሚያቀርብ ለቸችቱ አስረድቷል፡፡

በተጨማሪም በግንቦት ስምንቱ የአንደኛ ወንጀል ችሎት መቃወሚያ ባቀረቡት 21ኛ ተከሳሽ አቃቤ ህግ ምላሹን በጽሁፍ ያቀረበ ሲሆን፤ ጠበቆችም አቃቤ ህግ ለምስክሮች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ባቀረበው ማመልከቻ ላይ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት አስተያየታቸውን በተመሳሳይ በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በግምቦት 16፤ 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት አራት ትዕዛዞችን አስተላልፏል፡፡

1ኛ ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት ተከሳሾች ደመወዝ እየተከፈላቸው አለመሆኑን ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ያስተላፈው ትዕዛዝ ሲሆን፣ ጉዳዩ በመወንጀል ችሎት የሚታይ አይደለም ብሏል፡፡ ተከሳሾች የደመወዝ ይከፈለን አቤቱታቸውን ሊመለከት ወደሚችል ችሎት መውሰድ እንደሚችሉ አብራርቶላቸዋል፡፡

2ኛ በግንቦት ስምንቱ ችሎት መጥሪያ እንዲደርሳቸው የተሰጠውን ትዕዛዝ ሌላ ትዕዛዝ ሳያስፈልግ ፈደራል ፖሊስ እጁ የገባውን ትዕዛዝ ለአራቱም ተከሳሾች እንዲያደርስ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

3ኛ በማበዛት ስህተት ታትሞ ያልቀረበው ሲዲ ታትሞ ለተከሳሶች እና ፍርድ ቤት እንዲመጣ አንደኛው የወንጀል ችሎት ትዕዛዙን አስተላልፏል፡፡

4ኛ በ21ኛ ተከሳሽ ላይም ብይን ለመስጠጥት ለሰኔ 3፤ 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ ተጠናቋል፡፡