በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ኢንዲመለሱ እየተሰራ ነው

በየመን ኤደን አካባቢ የሚገኙ 2 ሺህ 44 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሀገሪቱ ያለውን አለመረጋጋትን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ኢንዲመለሱ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ኢንዲገቡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአይኦኤም እና በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃልአቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ከነዚህም ዜጎች መካከል 134 የሚሆኑት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ እንደሚገቡም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳጋቸው በጂቡቲ ሪፑብሊክና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በጂቡቲ ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸውን ቃልአቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

የሚኒስትሩ ቃልአቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በመግለጫቸው ግንቦት 17፤ 2011 ዓ.ም ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን የኢትዮጵያ አካል አድርጎ የሚያሳይ ካርታ በሚኒስቴሩ ድህረ ገጽ መውጣቱ ስህተት እንደነበር ገልጸው፣ መረጃው እንደታዬም መሥሪያ ቤቱ ማስተካከያ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡  

ስህተቱን በሰራው ል ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቆ በተፈጠረው ክስተት ሚኒስቴሩ መፀፀቱን ገልጸው ለዚህም ይቅርታ እንደጠየቀ አስታውቀዋል።