ኢትዮጵያና ጅቡቲ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለፁ

ከትላንት ጀምሮ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ስራቴጂክ ወዳጅነት ያላቸው አገራት ናቸው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ ወደፊትም በማናቸውም ፈታኝ ወቅቶች ግንኙናታቸው እንደማይሻክር እና ይልቁንም ይበልጥ እንደሚጠናከር ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው ያለውን ግንኙት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጅቡቲ ጋር ይበልጥ ተቀራርባ መስራት እንደምትፈልግ አቶ ገዱ ለፕሬዝዳንቱ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡