ጠ/ሚ ዐቢይ ከፍትሕ አካል አባላት ጋር እየተወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከመላ ሀገሪቱ ከተውጣጡ የፍትሕ አካላት አባላት ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ባለፈው አንድ ዓመት በዘርፉ የተካሄዱ የሕግ ማሻሻያዎች መሠረታቸውን በተቋማት ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

በተለይም አቅምን የመገንባትንና የመንግሥት ኃላፊዎችን ጨምሮ በሕግ የበላይነት የሚያምን ማኅበረሰብ የመፍጠርን አስፈላጊነት አስምረውበታል።

ከ3 ሺህ በላይ ዳኞች፣ ዐቃብያነ ሕግ፣ ጠበቆችና የፍትሕ ዘርፍ አመራሮች በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።