ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከጣልያን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ሲ ዴል ሪ ጋር ተወያዩ

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከጣልያን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ሲ ዴል ሪ ጋር ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ።

ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አዲስ አበባ የተገኙት የአክሱም ሐውልትን ለመጎብኘትና የእድሳቱን ዝርዝር አሠራርን ለመምከር ከመጣው የልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ነው።

ዴል ሪ በውይይታቸው የጣልያን መንግሥት በልዩ ልዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ ቀጣይነት አረጋግጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ የምትመራው የልዑካን ቡድኑ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቋቋም ያላትን ዝግጁነት በቴክኒክና በሰው ኃይል ዐቅም ግንባታ ዙሪያ ለመርዳት የሚወስን ይሆናል።