312 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – 312 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ለተመላሾቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡