የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት 62 አዋጆችና 2 ደንቦች ያጸደቀ ሲሆን 32 የውሳኔ ሐሳቦችንም ማሳለፉን አስታወቀ፡፡
ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠዉን ስልጣን መነሻ በማድረግ በዋና ዋና ተግባራት ላይ ዉጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡
አዋጆች እና ደንቦቹ ቀደም ሲል ከመጡ ህጎች ጋር የተጣጣሙ፣ ሕጎች ሲወጡ አስፈላጊ ሂደት በምክር ቤቱ በዝርዝር ተፈትሸዉ የሚመለከታቸዉ አካላት በስፋት የተሳተፉበት መሆኑን እና አንገብጋቢ የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎች የሚመለሱ ናቸዉ ብለዋል አፈ ጉባኤው፡፡
የክትትል እና ቁጥጥር ተግባራት ጋር በተያያዘ በምክር ቤቱ የሚገኙት 10 ቋሚ ኮሚቴዎች እና 33 ንዑስ ኮሚቴዎች በመስክ ምልከታ የተቋማት ስራ ክንዉን እና የሕጎች ተፈፃሚነትን ተከታትለዋል፡፡ የ25 ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን ለፓርላማ ሪፖርታቸዉ አቅርበዋል፡፡
የመራጭ እና ተመራጭ ግንኙነት እንዲሁም የፓርላማ የዲፕሎማሲ ሥራዎች ላይ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑን ምክር ቤቱ ጠቁሟል፡፡