ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባው በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል።

ጨፌው በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የቀረበለትን አዳዲስ የስራ ሀላፊዎችን ሹመት ተመልክቶ ነው ያፀደቀው።

በዚህም መሰረት፦

1. ዶክተር ሀብታሙ ኢተፋ፦ የኦሮሚያ ውሃ ቢሮ ሃላፊ

2. አቶ ዴንጌ ቦሩ፦ የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ሃላፊ

3. አቶ ግርማ ሀይሉ፦ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

4. አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፦ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሃላፊ

5. ዶክተር ቀነኣ ያደታ፦ የኦሮሚያ የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

6. አቶ ሳዳት ነሻ፦ የኦሮሚያ የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ

7. አቶ ሰይፈዲን ማሃዲ፦ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እና የጨፌ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ

8. ኢንጂነር ደጀኔ ፍቃዱ፦ ኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

9. ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ፦ የኦሮሚያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ

10. ዶክተር ቶላ በሪሶ፦ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ቦርድ ሰብሳቢ

11. አቶ ዝናቡ አስራት፦ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደሳ ቡልቻ የቀረበለትን 13 የዳኞች ሹመት ም ያጸደቀ ሲሆን፤ አዲስ የተሾሙ 13ቱ ዳኞች እና  የስራ ሃላፊዎች በጨፌው ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም ጨፌው በዛሬው ስብሰባው የክልሉ ዋና ኦዲተር አመራሮች እና ባለሙያዎች ጥቅማቅጥም ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ ላይ ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውል ማጽደቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡