በሱዳን የተደረገው ስምምነት የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን መፍታት እንደሚቻል በድጋሜ ያረጋገጠ ነው

በሱዳን የተደረገው ስምምነት የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን መፍታት እንደሚቻል በድጋሜ ያረጋገጠ ነው

የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ም/ቤት እና የነፃነትና የለውጥ ኃይሎች የደረሱበት ስምምነት የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን መፍታት እንደሚቻል እና ኢትዮጵያ በቀጠናው ሠላምና ጸጥታን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ም/ቤት እና የነፃነትና የለውጥ ኃይሎች የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ሕብረት የጋራ አደራዳሪዎች ባቀረቡት የስምምነት ሀሳብ ላይ በመወያየት ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የፓለቲካ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የተፈረመው የፖለቲካ ስምምነት የመንግስት አወቃቀር እና በሽግግሩ ወቅት ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የሚገዛ ሰነድ ነው።

በሱዳን የተከሰተውን ሕዝባዊ ተቃውሞና የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ም/ቤት እና የነፃነትና የለውጥ ኃይሎችን ለማቀራረብና የሲቪል መንግስት ለመመስረት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያስጀመሩት ጥረት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በተደረገ የተቀናጀ ጥረት ውጤት አስገኝቷል።

የድርድር ሂደት የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን መፍታት እንደሚቻል እና ኢትዮጵያ በቀጠናው ሠላምና ጸጥታን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠችበት ነው።