የአማራ ክልል ምክር ቤት አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ዛሬ ይሾማል

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የምክር ቤቱ ጉባኤ ሰኔ 15 2011 ዓ.ም ህይወታቸውን ላጡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው የተጀመረው፡፡

ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር፣4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ በባህር ዳር ማካሄድ የጀመረ ሲሆን ጉባዔው በዛሬው ውሎው የመደበኛ ጉባኤው አጀንዳዎችን እና የ12ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ ቀርበው የሚፀድቁ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል የተጓደለውን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድረነት ሹመትን በቀረቡት ዕጩ ላይ በዛሬው እለት ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የ2011 በጀት ዓመት የተጠቃለለ  የአስፈፃሚ አካላት የ11 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ሌላኛው በምክር ቤቱ ውሎ የሚታይ ጉዳይ ይሆናል፡፡