የድሬዳዋ ምክር ቤት አቶ አህመድ መሐመድ ቡህን ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾመ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ የስራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አህመድ ቡህን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾመ ።

ጉባኤው ካለፈው መጋቢት 2011 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በከንቲባነት ያገለገሉትን የአቶ መሐዲ ጊሬን መልቀቂያ ተቀብሎ በምትካቸው አቶ አህመድ ቡህን በምክትል ከንቲባነት ሾሟል።

በተጨማሪም ጉባኤው የአፈጉባኤ አብደላ አህመድን መልቀቂያ ተቀብሎ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጣፋን የአስተዳደሩ አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

ምክትል ከንቲባው ድሬዳዋ ለሁሉም የምትመችና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ተሰናባቹ ምክትል ከንቲባ በኃላፊነት በቆዩባቸው ወራት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃ  ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡የድሬዳዋ ከንቲባ ጽ/ቤት