የጥናት ቡድኑ የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ለመመለስ በተካሄደው ጥናት ላይ ማብራሪያ ሰጠ

የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ለመመለስ የኢህአዴግ ጉባኤ ያስተላለፈውን አቅጣጫ ተከትሎ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የጥናት ውጤቱን በትናንትናው እለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ለኢህአዴግ እና ደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም ለዞንና ወረዳ አመራሮች የጥናቱን ውጤት ይፋ ያደረገው ቡድኑ፤ዛሬ በጥናቱ ውጤት ከምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡

ከምክክሩ የሚገኙ ሀሳቦችን እንደግብዓት እንደሚጠቀምባቸው፤ በሂደትም ከህብረተሰቡ ጋር እስከ ቀበሌ ድረስ ውይይት እንደሚደረግ የቡድኑ ሰብሳቢ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡

በተዋረድ በሚደረጉ ውይይይቶች የሚገኙ ግብዓቶችን መሰረት በማድረግ በጥናቱ ውጤት ላይ በመመርኮዝ ቀጣይ የክልሉ ዕጣ ፈንታ  ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡