የአማራ ክልል ምክር ቤት የ230 ዳኞችን ሹመት አጸደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት የ230 ዳኞችን ሹመት አጸደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት በተለያዩ ደረጃዎች የሚመደቡ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፤ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ደግሞ ከሥራ አሰናብቷል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአራተኛ ቀን ውሎው ከሰዓት በፊት ከተመለከታቸው ጉዳዮች ውስጥ የዳኞች ሹመት ይገኝበታል፡፡

በዕጩነት የቀረቡት ዳኞች በሥነ ምግባራቸው ጥሩ ስለመሆናቸው አስተያዬት የተሰጠባቸው፣ በመመልመያ መስፈርቱ ተወዳድረው የተመረጡ እና የትምህርት ደረጃውንም ያሟሉ ናቸው ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት 10 ዳኞች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት፣ ሁለት ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትነት፣ 18 ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኝነት፣ 200 ዳኞች ለወረዳ ፍርድ ቤት ዳኝነት ተሹመዋል፡፡የሁሉም ዳኞች ሹመት በሙሉ ድምጽ ነው የጸደቀው፡፡

ምክር ቤቱ አምስት ዳኞችን በስነ ምግባር ጉድለት ከሥራ አሰናብቷል ሲልየዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙሀን ነው።