ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሊ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ለመቀጠል በሚችልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በምግብ ደህንነት፣በተመጣጠነ ምግብ፣ በአቅም ግንባታ ዘርፎች እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ኢትዮጵያን እየደገፈ መሆኑ ይታወቃል።

ከውይይቱ በኋላም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ መትከላቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።