የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከትናንት ነሓሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ኮሚቴው የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳች ላይ ውይይት እያደረገ ነው፡፡

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡